በምዕራብ ጎንደር ዞን ከ890 ሺህ በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ ኾነዋል።

11

ገንዳ ውኃ: ሰኔ 16/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዞኑ ይተከላል ተብሎ ከታቀደው 1 ሚሊዮን ችግኝ ውስጥ ከ890 ሺህ በላይ ችግኞች ለተከላ ዝግጁ መኾናቸውን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታውቋል። የደን ልማት ባለሙያው ጋሻው ታያቸው ለ2017/2018 ለችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ 558 ካሬ መሬት ዝግጁ መደረጉንም አብራርተዋል። በ30 የችግኝ ጣቢያዎች ችግኝ መፈላቱንም ባለሙያው አንስተዋል።

ለተከላ የተዘጋጁ የችግኝ ዓይነትም እንደሰርኪን፣ ዲዛ፣ ማንጎ፣ ኩመር፣ ሽመል (ቀርቀሃ)፣ አኬሻ ሴኔጋል፣ ዋንዛ፣ ጽድ እና ሚም እንደኾኑም ባሙያው ጠቅሰዋል። ከ100 በላይ የጉልበት ሠራተኞች በችግኝ ማፍላት ሥራው እንደተሳተፉም አስረድተዋል።

ችግኞች አሳሳቢ እየኾነ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር እና የደን ሃብትን ለመጨመር ዓይነተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋልም ብለዋል።ማኅበረሰቡም ችግኝ ከመትከል ባለፈ ለችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ እና ክትትል ማድረግን የዘውትር ልምዱ እንዲያደረግ ጠይቀዋል።ከባለፈው ዓመት ከተተከለው 642 ሺህ በላይ ችግኝ 474 ሺ በላይ ችግኝ መጽደቁንም አውስተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሀሰተኛ-ፍካት!
Next articleበተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ሥራዎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ይሠራል።