
ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በአዲስ ቅዳም ከተማ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ ጽንፈኝነትን አጥብቀን እናወግዛለን፣ ሰላምን እንሻለን፣ የጥይት ድምፅ መስማት አንፈልግም፣ ማኅበራዊ እረፍት እንሻለን፣ ከመንግሥት ጎን እንቆማለን፤ የሕግ ማስከበር ሥራውን እንደግፋለን፣ ልጆቻችንን ማስተማር እንፈልጋለን እና ሌሎች መሰል መልዕክቶች እየተሰሙ ነው።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
