በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።

71

ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር አንከሻ ጓጉሳ ወረዳ እና በአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳደር ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፉ የመንግሥትን ሕግ የማስከበር ሂደት እውቅና የሚሰጥ እና ጽንፈኝነትን የሚያወግዝ ነው።

በድጋፍ ሰልፉ ላይ ሰላምን እንሻለን፣ ጽንፈኝነትን እናውግዛለን፣ ከመንግሥት ጎን እንቆማለን፣ ወደ ልማት መግባት እንፈልጋለን፣ ለክልላችን ጦርነት ሳይኾን የሚያስፈልገው ሰላም እና ልማት ነው የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየእንጅባራ ከተማ ነዋሪዎች ፅንፈኝነትን የሚያወግዝ እና መንግሥት እየወሰደ ያለውን ሕግ የማስከበር ርምጃ የሚደግፍ ሰልፍ አካሂደዋል።
Next articleነገን ዛሬ መቅደም!