
ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የተለያዩ አካባቢዎች ጽንፈኝነት የሚያወግዝ እና ሰላምን የሚደግፍ ሕዝባዊ ሰላማዊ ስልፍ እየተካሄደ ነው።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ልጆቻችን ይማሩ፣ የመንግሥትን ሕግ የማስከበር እርምጃ እንደግፋለን፣ ጽንፈኝነትን እናወግዛለን እና መሰል መልዕክቶችን እያሰሙ መኾኑን ከብሔረሰብ አስተዳደሩ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!