በ185 ሚሊየን ብር ወጪ በአርቲስት እንየ ታከለ የተገነባው የባህል ምሽት ቤት ተመረቀ።

27

የባህል ምሽት ቤቱ የጎንደርን ታሪክ የሚመጥን እንደሆነ ተመላክቷል።

የባህል ምሽት የጎንደር ከተማ አሥተዳደርና የክልል የሥራ ኃላፊዎች መርቀው ከፍተዋል።

የቱሪዝም ማዕከል የሆነችውን ጎንደር ለማጉላት መሰል የባህል ምሽት ቤቶችን ለማስፋት እንደሚሠራም ተገልጿል።

የባህል ምሽት ቤቱ የጎንደር ከተማና የአካባቢው ባህል ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል የተናገረችው አርቲስት እንየ በተወለድኩበት አካባቢ የዘመናት ህልሜ በመሳካቱ ደስተኛ ነኝ ብላለች።

18 ደረጃቸውን የጠበቁ የመኝታ ክፍሎች ያሉት የባህል ምሽት ቤቱ ለ95 ወጣቶች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩ ተገልጿል።

Previous articleየረጅም ዘመን መዳረሻን ለማመላከት የረጅም ጊዜ ዕቅድ አስፈላጊ ነው።
Next articleተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ያገኙትን ዕውቀት በመጠቀም ማኀበረሰቡን ማገልገል ይጠበቅባቸዋል፡፡