ደንበኛ ተኮር እሴት በመከተል አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ ጥረት እየተደረገ ነው።

11

ደብረ ብርሃን፡ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ከቁልፍ ደንበኞች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ምክክር እያካሄደ ይገኛል።

የተሳታፊነት እና ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ደንበኞች በአገልግሎት አሰጣጡ ከፍተኛ እርካታ እንዲኖራቸው ለማስቻል እየተሠራ መኾኑን የገለጹት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ዳይሬክተር ሙሉጌታ ደሳለኝ ናቸው።

እንደ ተቋም ደንበኛ ተኮር እሴት በመከተል አገልግሎት አሰጣጡን ለማሳለጥ ጥረት እየተደረገ ስለመኾኑም አስገንዝበዋል።ዘመኑ የሚጠይቀውን አገልግሎት ለደንበኞች በፍጥነት እና ጥራት ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ ስለመኾኑም ጠቅሰዋል።

ቁልፍ ደንበኞችን በመለየት ለማገልገል የሚያስችል አደረጃጀት በመፍጠር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መኾኑን ተናግረዋል።ደንበኞችም የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የኀይል አቅርቦት እና ማስፋፊያ በሚሻሻልበት ኹኔታ ላይ የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።

ዘጋቢ፦ ዮናስ ታደሰ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
Next article“የነገ ሀገር የምትመስለው የዛሬ ተማሪዎችን ነው” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)