
ደብረ ታቦር: ሰኔ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ታቦር ዩኒቪርሲቲ በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ በተለያየ የትምህርት ዘርፎች ያስተማራቸውን 987 ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቀ ነው።በመጀመሪያ ዲግሪ 782፣ በሁለተኛ ዲግሪ 205 ተማሪዎችን ለ13ኛ ጊዜ እያስመረቀ ይገኛል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ፣ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ኃይለኢየሱስ ሰለሞንን ጨምሮ የተመራቂ ተማሪ ቤተሰቦች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በምረቃ ሦነ ሥርዓቱ የእንኳን ደኅና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የደብረ ታቦር ዩኒቪርሲቲ ፕሬዝዳንት ሰለሞን አበጋዝ (ዶ.ር) ይህ ወቅት ከአንዱ የሕይዎት ምዕራፍ ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ በመሸጋገር ከሕይወት የምትማሩበት እና ወደ ሌላኛው ትምህርት ቤት የምትገቡበት ወቅት ስለኾነ ማስተዋልን ይጠይቃል ብለዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።በመልክታቸውም በቀጣዩ የሕይዎት መንገዳችሁ እስካሁን የሰነቃችሁትን እውቀት በሥራ ላይ በማዋል ሀገርን እና ማኅበረሰብን ማገልገል ይገባችኋል ሲሉ ለተመራቂዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን