
ባሕር ዳር: ሰኔ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምረቃ በመርሐ ግብሩ ላይ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን መሐመድር (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳኅሉ (ዶ.ር) ፣ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ.ር)፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 6 ሺህ 174 ተማሪዎችን ነው ዛሬ እያስመረቀ የሚገኘው። ከተመራቂዎች ውስጥ 1 ሺህ 715 ተማሪዎች ሴቶች ናቸው።አጠቃላይ ከሚመረቁ ተማሪዎች መካከል111 የሚኾኑት በሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ናቸው። በሕክምናው ዘርፍ ደግሞ 90 ሐኪሞች በስፔሻሊቲ እንዲሁም ስምንት ሐኪሞች በሰብ ስፔሻሊቲ ተመራቂዎች ናቸው። ዛሬ ከሚመረቁት መካከል ዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ በዳታ ሳይንስ እና በሳይበር ደኅንነት በመጀመሪያ ዲግሪ ያሠለጠናቸውም ተማሪዎች ያስመርቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን