እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።

12

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም (አሚኮ) እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው፣ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች፣ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ተገኝተዋል።

ዩኒቨርሲቲው ለ6ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እያስመረቀ የሚገኘው። ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ሥራው ባሻገር በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የነቃ ተሳትፎ የሚያደርግ ዩኒቨርሲቲ ነው።
በአረንጓዴ ልማት እና ለሥራ የተመቸ ከባቢን በመፍጠርም የተመሰከረለት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ነው።

በታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleኢትዮጵያውያን ለግድቡ ግንባታ እውን መኾን ያደረጉት ተሳትፎ ግዙፍ የልማት ሥራዎችን በራስ አቅም መሥራት እንደሚቻል ለዓለም ያሳየ ነው።
Next articleእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው።