ከ821 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።

18

ደብረ ማርቆስ: ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በ2017 በጀት ዓመት ከ821 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ አስታውቋል። መምሪያው ከግብር አከፋፍል ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የውዝፍ ክፍያ ማስመለሱን ገልጿል።

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት ከመደበኛ እና መደበኛ ካልኾነ ገቢ ከ821 ሚሊዮን 895 ሺህ ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን የመምሪያው ኀላፊ ጌታቸው አለበል ተናግረዋል። መምሪያ ኅላፊው በክልሉ የተከሰተው የሰላም እጦት በገቢ አሠባሠቡ ላይ ከፍተኛ ችግር ማስከተሉን ጠቁመዋል።

ለማድረግ ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ የተለያዩ ሥራዎች እየሠራ መኾኑንም አስረድተዋል። ከግብር አከፋፍል ጋር ተያይዞ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት በተሠራው ሥራ ከ80 ሚሊዮን ብር በላይ የውዝፍ ክፍያ ማስመለሱን ጠቁመው በቀጣይም ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በመግባባት በአጭር እና በረጅም ጊዜ ያለባቸውን የውዝፍ ክፍያ እንዲከፍሉ ይደረጋል ነው ያሉት።

መምሪያው የ2018 በጀት ዓመት የጀረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮችን ግብር ከሐምሌ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለመሠብሠብ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በመሥራት ላይ መኾኑን የገለጹት አቶ ጌታቸው ግብር ከፋዩ ማኅበረሰብም ግብሩን በወቅቱ እንዲከፍልም አሳስበዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleክልሉ ባለፉት 14 ዓመታት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ ብር ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ አበርክቷል።
Next articleዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ስለ ሰላም መምከር ከቤት ይጀምራል።