ክልሉ ባለፉት 14 ዓመታት ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን በላይ ብር ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ አበርክቷል።

14

ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሕዝባዊ ድጋፍ አሰባሳቢ እና አሥተባባሪ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት የምስጋና እና እውቅና መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የአማራ ክልል ማስተባባሪያ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ዓባይነህ ጌጡ እንዳሉት የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የልማታችን ዋነኛ መሠረት ነው። የመልማት አቅማችን በራሳችን አቅም ያሳየንበት መኾኑንም ገልጸዋል። ኀላፊው እንዳሉት በ2017 ዓ.ም ብቻ 90 ሚሊዮን ብር ከማኅበረሰቡ ማሰባሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

ባለፉት 14 ዓመታት ደግሞ ለታላቁ ሕዳሴ ግድብ በክልሉ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ ድርጅቶች እና ልዩ ልዩ የገቢ ማስገኛ መንገዶች ወደ 1 ነጥብ 34 ቢሊዮን ብር ገንዘብ ተሰብስቧል። ግድቡ በደለል እንዳይሞላ የክልሉ ሕዝብ በአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራዎች ከፍተኛ የጉልበት አስተዋጽኦ አበርክቷል። ባለፉት 14 ዓመታት 38 ቢሊዮን ብር የሚኾን የጉልበት አስተዋጽኦ ማበርከቱን ነው ኀላፊው የገልጹት። በምስጋና እና እውቅና መርሐ ግብሩ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“የሥራ ውርሳቸው በሔራዊ ምልክቶች እና በሚወክሉት የእድገት ትእምርት ሲታወስ ይኖራል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleከ821 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሠብሠቡን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ።