
ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት በአማራ ክልል የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው። የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች እና አባላት ወደ ጎርጎራ አቅንተው እየተሠራ ያለውን የልማት እንቅስቃሴ መመልከታቸው ይታወሳል።
ዛሬ ደግሞ በባሕር ዳር ከተማ ተገኝተው በከተማዋ በተለይም በጣና ሐይቅ ዳርቻ ላይ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል። የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም መሪዎች እንግዶችን ተቀብለዋል።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን