
ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙት ሴት አምባሳደሮች የባሕር ዳር ከተማን የልማት ሥራዎች ጎብኝተዋል። በባሕር ዳር ከተማ በሰላም ግንባታ እና ግጭት አፈታት ዙሪያ ሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙት ሴት አምባሳደቹ በከተማዋ የተሠሩ የልማት ሥራዎችን ነው የተመለከቱት።
በጉብኝቱ ላይ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ኀላፊ ጊዜው ታከለ ተገኝተው በከተማዋ እየተከናወኑ ስላሉት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለጎብኝዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በከተማዋ እየለሙ ያሉት የልማት ሥራዎች የሚበረታቱ መኾናቸውን ነው ጎብኝዎች የገለጹት።
የሚሠሩት ልማቶች ታሪካዊ እና ታዋቂ በኾኑ ከተማውን እና ሕዝቡን በሚገልጹ ስያሜዎች ቢሰየሙ ሲሉ ጎብኝዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። በከተማዋ የሕዝቡን እና የአካባቢውን ወግ፣ ባሕል እና ታሪክ የሚገልጹ ስያሜዎችን ለመሰየም ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ መኾኑንም አቶ ጊዜው ታከለ ጠቁመዋል። በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙት የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ሰላምን በማጽናት ሁሉም ኅብረተሰብ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባው አመላክተዋል።
ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን