በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ እንደሚሠሩ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ገለጹ።

20

ጎንደር: ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከሀገሪቱ ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና መሪዎች የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርትን ጎብኝተዋል። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሠብሣቢ ሰለሞን አየለ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የተጀመሩ የልማት ሥራዎች የሚበረታቱ ናቸው ብለዋል።

የተጠናቀቁ የልማት ሥራዎች ለታለመላቸው ተግባር እንዲውሉ ሰላም እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲኖር የጋራ ምክር ቤቱ ይሠራል ነው ያሉት። ከኹሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት በጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ቆይታቸው ደስተኛ መኾናቸውንም ተናግረዋል።

በዞኑ ያሉ የቱሪዝም ቦታዎችን በበቂ ሁኔታ ለማስተዋወቅ እየተሠራ መኾኑን በጉብኝታቸው መታዘባቸውንም አስረድተዋል። በጎንደር ከተማ ሰባት በዩኔስኮ የተመዘገቡ ቅርሶች መኖራቸውን የነገሩን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ያለው የጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት ለጎብኝዎች ተጨማሪ መዳረሻ ይኾናል ብለዋል።

ከጎንደር ከተማ በቅርብ ርቀት ያሉ የመዝናኛ እና የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች ጎብኝዎች የቆይታ ጊዜያቸውን እንዲያራዝሙ እንደሚያግዝም ተናግረዋል። በዞኑ ያሉ የቱሪስት መዳረሻ ሥፍራዎች ለጎብኝዎች ምቹ እንዲኾኑ የጸጥታ ሥራው ላይ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን የተናገሩት ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የመሬት መምሪያ ኀላፊ አላምረው አበራ ናቸው።

ዘጋቢ፦ አዲስ ዓለማየሁ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ጥገና እንደሚሰጥ አስታወቀ።
Next articleሥልጠና እየወሰዱ የሚገኙት ሴት አምባሳደሮች የባሕር ዳር ከተማን የልማት ሥራዎች ጎበኙ።