
ባሕር ዳር: ሰኔ 13/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተደጋጋሚ የነጻ የዓይን ሕክም ሲሰጥ ቆይቷል። ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 28/2017 ዓ.ም “ላይት ፎር ዘወርልድ” ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባባር ነጻ የዐይን ሞራ ቀዶ ጥገና እንደሚሠጥ በሆስፒታሉ የዐይን ሕክምና ክፍል አሥተባባሪ ድረስ ዓለማየሁ ገልጸዋል።
ከሰኔ 16/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም በፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሕክምናው የልየታ ሥራ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። ከሰኔ 21/2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም ደግሞ በፎገራ ወረዳ ቁሀር ጤና ጣቢያ፣ ሞጣ ጤና ጣቢያ፣ አዲስ ቅዳም ጤና ጣቢያ፣ በግምጃ ቤት ጤና ጣቢያ እና ቻግኒ ጤና ጣቢያ የልየታ ሥራ እንደሚሠራ ተገልጿል። ማኅበረሰቡም ጉዳዩን በመረዳት ችግሩ ያለባቸው ሰዎች በተጠቀሱት ቦታዎች እንዲመዘገቡ እገዛ እንዲያደርግም አሳስበዋል።
ዘጋቢ፡ ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን