ሴቶች ለሰላም ግንባታ ስለሚኖራቸው ሚና ያተኮረ ሥልጠና በባሕር ዳር ከተማ እየተሰጠ ነው።

11

ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “ሴት የሰላም አምባሳደሮችን ማደራጀት ለዘላቂ ሰላም ግንባታ” በሚል መሪ መልዕክት በአማራ ክልል በተለያዩ አደረጃጀቶች እየተሳተፉ ለሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ነው በባሕር ዳር ከተማ ሥልጠና እየተሰጠ የሚገኘው።

በሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ላይ በአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር)፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሴቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኢሌኒ ዓባይ እና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ከምሥራቅ ጎጃም ዞን፣ ከደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር፣ ከምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር፣ ከሰሜን ጎጃም ዞን እና ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ የማኅበረሰብ ወካይ ሴቶች በሥልጠናው እየተሳተፉ ነው።

እየተሰጠ ያለው ሥልጠና ሴቶች ለሰላም ግንባታ ስለሚኖራቸው ሚና ያተኮረ ነው። ሥልጠናው በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ሴቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ከዋናው የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት እና ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲኾን ለቀጣይ ሁለት ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleወልድያ ዩኒቨርሲቲ በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የቀዶ ጥገና ሕክምና እየሰጠ ነው።
Next articleከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ፈተናዎችን በፍጥነት ለመቅረፍ ትኩረት ያደረገ ጉባኤ ሊካሄድ ነው።