ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት የቀዶ ጥገና ሕክምና እየሰጠ ነው።

16

ወልድያ: ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የወልድያ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማኅበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አማረ ቢኾን (ዶ.ር) ዩኒቨርሲቲው ከወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ከወልድያ ደም ባንክ ጋር በመተባበር ሕክምናውን እየሰጠ መኾኑን ገልጸዋል።

በወልድያ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህር እና የዘመቻው አስተባባሪ ዘላለም ደጅአዝማች ከዩኒቨርሲቲው 20 የሕክምና ባለሙያዎች ያሉት ቡድን መሰማራቱንም ነግረውናል። በተጨማሪም የቅድሚያ ደም ማሠባሠብ ተግባር ላይ ከወልድያ ደም ባንክ ጋር በመቀናጀት ግምባር ቀደም ተሳትፎ አድርጓል ነው ያሉት። ዘመቻው እስከ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

የወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አሥኪያጅ ፍስሀ የኋላው በዘመቻው 216 ታካሚዎች ተደራሽ ይኾናሉ ብለዋል። ታካሚዎቹ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት የቀዶ ጥገና ቀጠሮ የነበራቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች ሕክምና ሳያገኙ የቆዩ መኾናቸውን ነግረውናል።

ታካሚዎቹ በዘመቻው አገልግሎት ማግኘታቸው ከሕመም እና በቀጠሮ ከሚደርስባቸው አላስፈላጊ ወጭ መታደግ ስለመቻሉም ነው የተገለጸው። የቀጠሮ ታካሚዎችን ቁጥር ዜሮ በማድረግ ከአሁን በኋላ የሚመጡ የቀዶ ጥገና ታካሚዎች በመጡበት ጊዜ ወዲያው ሕክምና አግኝተው እንዲመለሱ ያደርጋል፤ የታካሚዎችን የአገልግሎት እርካታም ይጨምራል ብለዋል። የሕክምና አገልግሎቱን ያገኙ ታካሚዎች በቀጠሮ ሲጉላሉ እንደነበር ገልጸው አሁን ላይ ፈውስን በማግኘታቸው መደሰታቸውን ነግረውናል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ ሴት መሪዎች የባሕር ዳር ከተማን የልማት ሥራዎች ጎበኙ።
Next articleሴቶች ለሰላም ግንባታ ስለሚኖራቸው ሚና ያተኮረ ሥልጠና በባሕር ዳር ከተማ እየተሰጠ ነው።