
ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ሥልጠና ሲወስዱ የቆዩ ከወረዳ እና ከዞኖች የመጡ ሴት መሪዎች በከተማዋ የተሠሩ የኮሪደር እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል። መሪዎቹ በጉብኝታቸው ተሞክሮዎችን ሊወስዱባቸው የሚችሉ በሴቶች እየተሠሩ ያሉ የከተማ ግብርና ሥራዎችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ ላይ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው የተገኙ ሲኾን በከተማዋ እየተከናወኑ ስላሉት የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለጎብኝዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የባሕር ዳር ከተማ ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ ሰብለ ዘውዱ በሴቶች እየተሠሩ ስላሉ የከተማ ግብርና ሥራዎች እና በከተማ አሥተዳደሩ እየተደረገ ስላለው ድጋፍ ለጎብኝዎች ገለጻ አድርገዋል።
ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን