በ24 ሰዓታት ውስጥ በ137 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል፡፡

252

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 21/2012 ዓ.ም (አብመድ) የጤና ሚኒስቴር በማኅበራዊ ገጹ እንደገለጸው ባለፉት 24 ሰዓታት ለ5 ሺህ 15 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ በ137 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል፤ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥርም 968 ደርሷል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 137 ሰዎች መካከል 109 የውጭ ሀገር ጉዞም ሆነ አስቀድሞ በቫይሱ መያዙ በሕክምና ከተረጋገጠ ሰው ጋር ንክኪ የሌላቸው ናቸው፡፡ 20ዎቹ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ሲኖራቸው ስምንት ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው አስቀድሞ ከታወቁ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብሏል፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 109 ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው፤ አንድ ሰው ከአፋር፣ ሁለት ሰዎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ 17 ከአማራ እና ስምንት ሰዎች ከኦሮሚያ ክልሎች ናቸው፡፡

ዛሬ ቫይረሱ የተገኘባቸው 86 ወንዶች እና 51 ሴቶች ሲሆኑ አንድ የ62 ዓመት አዛውንት በተጓዳኝ ሕመም ሕክምና ላይ እያሉ የተወሰደላቸው የኮሮናቫይረስ ምርመራ ናሙና ተወስዶላቸው የምርመራ ውጤት ከመድረሱ በፊት ሕይወታቸው አልፏል፤ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው እንደነበርም ውጤታቸው አረጋግጧል፡፡

ባለፉት 24 ሰዓታት አዲስ ስድስት ሰዎች ከአዲስ አበባ ማገገማቸውም ታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ እስከዛሬ ለ101 ሺህ 581 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ አድርጋ በ968 ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን አረጋግጣለች፤ 197 ሰዎች አገግመዋ፤ 8 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፤ 761 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ሕክምና ክትትል ውስጥ ናቸው፤ አራቱ በጽኑ ሕሙማን መከታተያ ውስጥ ናቸው፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ማጠናቀቅ ጀመሩ፡፡
Next articleበ115 ሚሊዮን ብር ሊገዛ የነበረው ፋብሪካ 315 ሚሊዮን ብር ውል ተይዞበታል፤ የፋይናንስ ችግርም ገጥሞታል፡፡