
ደብረ ማርቆስ: ሰኔ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በግጭቱ ምክንያት ጉዳት ያጋጠማቸውን የትምህርት ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች ለመጠገን እና ገጽታቸውንም ለማሻሻል እየሠራ መኾኑን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ አስታውቋል።
የምሥራቅ ጎጃም ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ጌታሁን ፈንቴ በበጀት ዓመቱ ከ200 በላይ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል። በዞኑ በግጭቱ ምክንያት ወደ ሥራ ያልገቡ የትምህርት ተቋማትን ለመክፈት ከኅብረተሰቡ ጋር ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል።
ዞኑ በጸጥታ ችግር ውስጥም ኾኖ ያስተማራቸውን ተማሪዎች የክልል አቀፍ ፈተና እንዲወስዱ ማድረጉን ያነሱት ኀላፊው የሀገር አቀፍ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎችም አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።
ጉዳት የደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች አስፈላጊው ጥገና ተደርጎላቸው ወደ መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ እንዲገቡ እየተሠራ መኾኑንም አንስተዋል። ለዚህ መልካም ተግባር ሁሉም አካል ድጋፉን እንዲሰጥም ጠይቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን