“የፖለቲካ ምኅዳርን መክፈት በ2010 ዓ.ም የወሰንነው ቁልፍ ውሳኔ ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ድ.ር)

23

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው “የፖለቲካ ምኅዳርን መክፈት በ2010 ዓ.ም የወሰንነው ቁልፍ ውሳኔ ነው” ሲሉ አስፍረዋል። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ረጅም ዘመን ከኖረው ፓርቲዎችን ተቃዋሚ አድርጎ ከመመልከት ሕጋዊ ተፎካካሪዎች አድርጎ በማስተናገድ ዴሞክራሲያዊ ከባቢን ለመፍጠር አበክረን ሠርተናል ሲሉም ጠቅሰዋል። ይህ የአስተሳሰብ ሽግግር ሰላማዊ የፉክክር ባሕል ለኢትዮጵያ መፃዒ ተስፋ አስፈላጊ መኾኑን በማመን ላይ የተመሠረተ ነበርም ብለዋል።

በዚሁ አቋም ተመርተንም ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተመዘገቡ ፓርቲዎች ጋር ተከታታይ መድረኮችን አስቀጥለን ቆይተናል። ዛሬም በሰሞኑ የሚካሄዱት የባለድርሻ አካላት ውይይቶች አካል የሆነ ውይይት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ይህም ከየመጡበት አካባቢ የሚነሱ የተለያዩ ሀሳቦችን በማዳመጥ ግብዓት ለመውሰድ የታለመ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒሰትሩ ትሩ ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ከተማዋን የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ማዕከል የሚያደርጉ መኾናቸውን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
Next article“እንግዳ ተቀባዩ የጅማ ሕዝብ ላደረገልን የሞቀ አቀባበል እናመሰግናለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ