
ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ጎብኝተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በጅማ ዞን ሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ የሻይ ቅጠል ልማትን ጎብኝተናል ብለዋል።
የአካባቢን ጸጋ ለይቶ ከራስ የተሻገረ፤ ሀገርን በሚጠቅም ትጋትና ቁርጠኝነት በልማት መገኘት እያመጣ ያለውን ውጤት በተጨባጭ እየታዬ መኾኑን ገልጸዋል። በጉብኝታችን የገጠር አካባቢን ምቹ እና እያዘመነ የሚገኘውን ኮሪደር ልማት ተምሳሌት የሚሆን ሥራ ተመልክተናል ነው ያሉት። በጽናት የመሥራት፣ በማሳ የመተጋገዝ ባሕል በሁሉም አካባቢ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።
አካባቢው የሚታወቅበትን የሻይ ቅጠል ልማት የሚያበረታታ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በጅማ ዞን ሰቃ ጮቆርሳ ወረዳ ከነዋሪዎች ጋር በጋራ አከናውነናል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን