አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኙ።

31

ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛ እና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ጄ ትራምፕ ጋር በነጩ ቤተመንግሥት ተገናኝተዋል።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ነጩ ቤተመንግሥት ሲደርሱ በኢትዮጵያ እና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚያንጸባርቅ ዲፕሎማሲያዊ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ከ120 ዓመታት በላይ የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት አላቸው። በሁለቱ ሀገራት መካከል እንደ ሰላም፣ ጸጥታ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ አጋርነት ከመፍጠር አንጻር ያሉ ዕድሎችም ሰፊ ናቸው።

አምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም በውይይቱ ወቅት ከስቴት ሴክሬተሪ ማርኮ ሩቢዮ ጋርም መገናኘታቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የቀደመ ታሪኳን የበለጠ የሚያደምቅ ሥራ ጅማ ላይ እየተሠራ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next article“በጽናት የመሥራት፣ በማሳ የመተጋገዝ ባሕል በሁሉም አካባቢ አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ