“የቀደመ ታሪኳን የበለጠ የሚያደምቅ ሥራ ጅማ ላይ እየተሠራ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

24

ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የትናንቱን የጅማ ዕሴት የሚጠብቁ፣ የነገውን ዘመን የሚዋጁ አስደናቂ ሥራዎች ዕውን እየተደረጉ መኾኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ተናገሩ።

‎ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት በጅማ ዞን የገጠር ኮሪደር ልማት፣ የከተማ ኮሪደር ልማት፣ የአባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ዕድሳት እና የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አስደማሚ ሥራዎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

‎በዞኑ ወደ ማና ወረዳ አቅንተን የቡና፣ የሻይ ቅጠል፣ የማር እና ሌሎች የቅርንጫፍ ልማቶችን እንዲሁም በገጠር ኮሪደር ለሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ሞዴል የኾነ እና ተግባር ተኮር ሥራን በማየቴ ኩራት ተሰምቶኛል ብለዋል።

‎የኢትዮጵያን ትንሳኤ የምናረጋግጠው ሌት ተቀን በመሥራት ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደረስንበት እና ያገኘነው ሳያዘናጋን ለነገ ሰፊ የመልማት ጸጋችን የቀጠለ ትጋት ያስፈልጋል ነው ያሉት።

‎እንደ ሀገር እየተከልነው ያለነው ልማትን ጀምሮ የመጨረስ ባሕላችን የሚጨበጥ፤ በተግባር የታየ አብነት፤ ለነገ የሚሻገር አሻራ ነው። ጅማዎችም ይሄን ዕውን ለማድረግ ትልቅ ትግል ላይ መኾናቸውን በማዬቴ እጅግ ደስ ብሎኛል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበባሕር ዳር ከተማ የተሠሩ የልማት ሥራዎች የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ጥራት የሚያሳድጉ መኾናቸውን የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገለጹ።
Next articleአምባሳደር ብናልፍ አንዱዓለም ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ተገናኙ።