
ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ከተለያዩ ክልሎች እና የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ባሕር ዳር ከተማ ገብተዋል። ባለሙያዎች ባሕር ዳር ከተማ ሲደርሱ የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የባሕር ዳር ከተማን የልማት ሥራዎች ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጣና ሐይቅ ላይ የሚገነባውን ጣና ማሪና ሪዞርት፣ አዲሱን የዓባይ ድልድይ፣ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ የኮሪደር ልማት እና ሌሎችንም የልማት ሥራዎች ነው ተዘዋውረው የተመለከቱት።
ባለሙያዎች ባሕር ዳር ከተማ ሰላሟን አሥጠብቃ እየለማች የምትገኝ የቱሪዝም ከተማ መኾኗን በጉብኝታቸው ወቅት ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
