
ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ለአማራ ክልል ሴት መሪዎች ከቀውስ ማገገሚያ እና የቀውስ ጊዜ አመራር ሥልጠና በባሕር ዳር ከተማ እየተሰጠ ነው።
በሥልጠና ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ ብርቱካን ሲሳይ፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ሥልጠናው በአማራ ክልል ሴቶች ሕጻናት እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና ስሪአር ፎር ሲኤሲኢ (3R _ 4 _ CACE) ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው።
በሥልጠናው ከምሥራቅ ጎጃም፣ ከምዕራብ ጎጃም፣ ከአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር፣ ከደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር፣ ከደቡብ ጎንደር ዞን፣ ከደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር፣ ከሰሜን ጎጃም ዞን እና ከባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የተውጣጡ 230 ሴት መሪዎች ተሳታፊዎች ናቸው።
ሥልጠናው ለቀጣይ ሁለት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል።
ዘጋቢ:- ፍሬሕይዎት አዘዘው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
