መለው ኢትዮጵያውያን ብሔራዊ ቤተ መንግሥትን እንዲጎበኙ ጥሪ ቀረበ።

15

አዲስ አበባ: ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ ቤተ መንግሥት ለሕዝብ ክፍት ኾኗል። የብሔራዊ ቤተ መንግሥትን ለሕዝብ ክፍት መኾንን በማስመልከት መግለጫ የሰጡት በሚኒስቴር ማዕረግ የቤተ መንግሥት አሥተዳደር ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ዴሬሳ የብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ ለሕዝብ ክፍት መኾን ኢትዮጵያ ያላትን ፀጋ የመግለፅ ውጤት ነው ብለዋል።

በቤተ መንግሥቱ በርካታ ታሪካዊ እና ውድ ነገሮች እንደሚገኙ ገልጸዋል። በውስጡም:-
👉 የጥንታዊ እና ውድ የኾኑ መኪኖች ሙዚየም
👉 የነገሥታት እና ፕሬዝዳንት መጠቀሚያ የነበሩ ቁሶች
👉 ከተለያዩ የዓለም መንግሥታት የተበረከቱ ስጦታዎች እና መሰል ታሪካዊ ቅርሶች ይገኛሉ ብለዋል።

በተጨማሪም ከዚህ በፊት የብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ አካል የነበሩ እና ለባለሀብቶች ተላልፈው ተሰጠው የተገነቡ የሬስቶራንት እና የተለያዩ የመዝናኛ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትም ይገኛሉ ብለዋል።መላው ኢትዮጵያን ብሔራዊ ቤተ መንግሥቱን በመጎብኘት ልምድ እንዲወስዱ እና ለትውልድ እንዲያሻግሩ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ብሔራዊ ቤተ መንግሥቱ ለጉብኝት ክፍት የሚኾነው ከማክሰኞ ውጭ ባሉ ቀናት ከጥዋቱ 3:00 እስከ ቀን 11:30 መኾኑን ገልጸዋል። የመዝናኛ እና የሬስቶራንት አገልግሎቶች ደግሞ እስከ ምሽት 3 ሰዓት ክፍት ይኾናሉ ብለዋል።በቀጣይም መንግሥት በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ ታሪካዊ አብያተ መንግሥታትን በማደስ ለጎብኝዎች ክፍት በማድረግ ዘርፉን ለማሳደግ ይሠራል ብለዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ
Next articleበዓመቱ ከ325 ቶን በላይ የማር ምርት መመረቱን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር አስታወቀ።