ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጅማ ገቡ።

14

ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎች ላይ ለመታደም ጅማ ገብተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልዕክት ለዘመናት የኅብረ ብሔራዊነት መናኸሪያ በኾነችው በአባ ጅፋር ሀገር፣ በንግድ፣ በባሕል፣ በሃይማኖት እና በትምህርት ኢትዮጵያውያን ከአራቱም ማዕዘን ሲገናኙባት የኖረች ከተማ ጅማ ገብተናል ብለዋል።

በታሪካዊቷ ከተማችን ለስድስተኛ ጊዜ የሚካሄደውን ሀገር አቀፍ የመላው ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን እናስጀምራለን ነው ያሉት። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው ጅማ ከተማ ስንደርስ ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን የፌደራል አመራሮች፣ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች እና የጅማ እና አካባቢው ነዋሪዎች ሁሉ የከበረ ምስጋና አቀርባለሁ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአፍሪካ ሀገራት ለኀይል አቅርቦት ቅድሚያ ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል።
Next articleየሰራዊቱ እና የክልሉ የጸጥታ ኃይል የተቀናጀ ስምሪት ውጤት ማምጣቱን ሌተና ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ተናገሩ።