የአፍሪካ ሀገራት ለኀይል አቅርቦት ቅድሚያ ሰጥተው ሊሠሩ ይገባል።

13

አዲስ አበባ: ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አራተኛው የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በኀይል አቅርቦት እና በተፋሰስ ልማት ላይ የሚመክረው ኮንፈረንሱ ዘንድሮ ቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ኀይል ግንባታ ለዘላቂ እና አስተማማኝ ልማት በሚል መሪ መልዕክት ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ቀጣናዊ ትብብርን እና መናበብን በማምጣት የኀይል አቅርቦትን ማረጋገጥ ላይ መሪዎች እንዲሠሩ ለማንቃት ያለመ ነው። ይህ ለቀጣናው ልማት እና ብልጽግና ወሳኝ ነው ተብሏል። በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ ቀጣናዊ ድርጅቶችን ጀምሮ መንግሥታት ለኀይል አቅርቦት ሊሠሩ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበው ኢትዮጵያ ለዘርፉ ትኩረት መስጠቷን ጠቅሰዋል።

በምሥራቅ አፍሪካ በርካታ ነዋሪዎች የኀይል አቅርቦት ችግር አለባቸው። የኀይል አቅርቦት ደግሞ እንደምግብ ሁሉ የግድ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ኀይል የሌለው ሀገር ስለኢንዱስትሪ እና ስለልማት ማውራት የማይችል በመኾኑ ለዚህ መትጋት ይገባል ብለዋል።

በኮንፈረንሱ ላይ የውኃና ኢንርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ኢተፋ፣ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ጃፋር በድሩ፣ የናይል ተፋሰስ ሀገራት ኢኒቨቲቭ ኀላፊ በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደርን ጨምሮ ሌሎች ንግግር አድርገዋል። በኮንፈረንሱ የፓናል ውይይቶችም ይከናወናሉ።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleሀገራዊ ቅርሶች በሕግ ዐይን።
Next articleምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጅማ ገቡ።