ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትን የለውጥ ሥራዎች ተመለከቱ።

26

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎችም የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ መሪዎች የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የለውጥ ሥራዎችን ተመልክተዋል።

 

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የመሥሪያ ቤት ሕንጻውን በዘመናዊ መልኩ አድሷል። የፍትሕ ሥርዓቱ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና የክልሉን ሕዝብ የሚመጥን እንዲኾንም የማሻሻያ ሥራዎችን እያከናወነ ነው።

 

ለዚህም የመሥሪያ ቤት ሕንጻውን ለደንበኞች እና ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ከማድረግ በተጨማሪ የቴክኖሎጅ አቅሙን በማሳደግ ደንበኞቹ ባሉበት ኾነው የችሎት አገልግሎት የሚያገኙበትን አሠራር ዘርግቷል።

 

ከፍተኛ መሪዎች የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን የለውጥ ሥራዎች ነው የተመለከቱት።

 

ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበሥነ ምግባር የተቃኘ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም ሕጻናት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ
Next articleጎንደር ትናንትን ከዛሬ፣ ዛሬን ከነገ ያስተሣሠረች እና ሕልም በተግባር የተገለጠባት ከተማ መኾኗን የጥበብ ባለሙያዎች ተናገሩ።