ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ለማሳደግ እየሠራ መኾኑን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አስታወቀ።

15
ከሚሴ: ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጤና መምሪያ በጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በጤናው ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በርካታ ሥራዎች መሠራቱን ገልጸዋል። አዲሱ ፍኖተ ካርታ ከተደራሽነት እና ፍትሐዊነት አንፃር የሚነሱ ክፍተቶችን የሚያሻሽል ነው ብለዋል።
በዚህም የመድኃኒት አቅርቦት እና መሰል የሚነሱ ችግሮችን በመቅረፍ አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል እንደሚሠሩ ተናግረዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ ኡስማን አሊ ውይይቱ አዲሱን የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያስችል ነው ብለዋልአዲሱ የጤና ኤክስቴሽን ፍኖተ ካርታ የጤና አገልግሎትን ፍትሐዊነት እና ተደራሽነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መኾኑንም ተናግረዋል።
የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ አህመድ አሊ በሀገራችን የጤና ኤክስቴሽን መርሐ ግብር ላለፉት 20 ዓመታት ሲተገበር መቆየቱን ጠቅሰዋል። በአዲሱ የጤና ኤክስቴሽን ፍኖተ ካርታ የማኅበረሰቡን የጤና ሽፋን በማሳደግ የጤና ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካት መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
ቅድመ መከላከልን መሠረት ያደረገ የጤና ኤክስቴንሽን ተግባራዊ በማድረግ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጤና ተቋማት እና ባለሙያዎች ሊሠሩ ይገባልም ብለዋል።
የማኅበረሰቡ ጤና ለማረጋገጥ ባለፉት 20 ዓመታት የመጣንባቸውን ስኬቶች በማስቀጠል ጥራት ያለው እና ፍትሐዊ የኾነ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በቀጣይ በቅንጅት መሥራት ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሒም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleአረንጓዴ ልማት በኢትዮጵያ
Next articleበሥነ ምግባር የተቃኘ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለመፍጠር ሁሉም ሕጻናት ላይ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ