የፌዴራል መንግሥት እና የክልል ከፍተኛ መሪዎች የባሕር ዳር ከተማ የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው።

20
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታየ አጽቀሥላሴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ ሚኒስትሮች እና ሌሎችም መሪዎች በባሕር ዳር ከተማ ተገኝተዋል።
የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ መሪዎች ባሕር ዳር ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ከፍተኛ መሪዎች እና የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች፣ የከተማዋ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ወጣቶች እና ሌሎችም ነዋሪዎች ተቀብለዋቸዋል።
መሪዎቹ በከተማዋ ተዘዋውረው የልማት ሥራዎችን እየተመለከቱ ነው። መሪዎቹ በጣና ሐይቅ ላይ የሚገነባውን ጣና ማሪና ሪዞርት፣ አዲሱን የዓባይ ድልድይ፣ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም፣ የኮሪደር ልማት እና ሌሎችንም የልማት ሥራዎች ነው ተዘዋውረው እየተመለከቱ የሚገኙት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበዕውቀት፣ በክህሎት እና በተነሳሽነት የተገነባ አገልጋይ የሰው ኀይል ማልማት ተገቢ ነው።
Next articleዕውቀትን፣ ቴክኖሎጂን እና ክህሎትን መሠረት ያደረጉ ማሻሻያዎች በማከናወን የአገልግሎት አሰጣጡን ማሳለጥ ይገባል።