የአፍሪካ አቬዬሽን ማኅበር የአፍሪካውያን ድምጽ ተሰሚነት እንዲኖረው ማድረግ ችሏል።

15
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ አቬዬሽን ማኅበር 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ በዓሉን በአዲስ አበባ እያከበረ ነው።
የአፍሪካ አቬዬሽን ማኅበር የብር ኢዮቤልዮ በዓል በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን “የ25 ዓመታት የልህቀት ጉዞ በአፍሪካ ሥራ ተኮር ግምገማ ጠንካራ የወደፊት አብሮ መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1999 በ40 የአፍሪካ ሀገራት የተመሠረተው የአፍሪካ አቬዬሽን ማኅበር ከ3ሺህ በላይ አባላትን ማፍራት ችሏል።
ማኅበሩ ባለፉት ዓመታት ጉዞው በአቅም ግንባታ፣ በዕውቀት ልውውጥ እና በመረጃ ላይ የተመሠረተ የፖሊሲ አወጣጥ ላይ ትኩረት ያደረጉ በርካታ ሥራዎችን ሠርቷል።
ማኅበሩ በየሁለት ዓመቱ በሚያደርጋቸው ጉባኤዎችም አፍሪካን መሠረት ያደረጉ የአሠራር ዘዴዎች ዕውቅና እና ዋጋ እንዲኖራቸው ማድረግ ችሏል።
ዓለም አቀፋዊ የግምገማ ስኬቶችን በመቅረጽም የአፍሪካውያን ድምጽ ተሰሚነት እንዲኖረው ማድረግም ችሏል። 25ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉ ላይ ከ300 በላይ ተሳታፊዎች የታደሙ ሲኾን የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎች እና የልማት ድርጅቶችም ተሳታፊ ናቸው።
የኢዮቤልዮ በዓሉ ከኢትዮጵያ ኢቬዬሽን ማኅበር፣ ከፕላን እና ልማት ሚኒስቴር እንዲኹም ከሌሎች የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት መዘጋጀቱም ተገልጿል።በዓሉ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቀጥል ሲኾን የተለያዩ መርኃ ግብሮችም ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታስተናግዳለች” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleበዕውቀት፣ በክህሎት እና በተነሳሽነት የተገነባ አገልጋይ የሰው ኀይል ማልማት ተገቢ ነው።