
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመተባበር ሁለተኛውን የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ እንደምታስተናግድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
የሰው ዘር መገኛ የኾነችው ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ታስተናግዳለች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉባኤው ለሰው ልጅ ተስማሚ የኾነ አካባቢ ለመፍጠር የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!