
ጎንደር: ሰኔ 08/2017 ዓ.ም (አሚኮ)የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የገነባቸውን የተለያዩ ፕሮጀክቶች መርቀው ሥራ አሥጀምረዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ሚኒስትሮች እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት ዓመታት ያሠራቸውን 22 ፕሮጀክቶች ነው ዛሬ አሥመርቆ ሥራ ያስጀመረው። ለዓመታት የተሠሩት ፕሮጀክቶች አንጋፋው ዩነቨርሲቲ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ፣ ተደራሽነቱ እንዲሠፋ እና የመማር ማስተማር ሥራው የዘመነ እንዲኾን የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!