“የሕፃናትን መብት እና ደኅንነት ማስጠበቅ የሁልጊዜም ተግባራችን ሊኾን ይገባል”

17

ደብረ ብርሃን: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በደብረ ብርሃን ከተማ የዓለም ሕፃናት ቀን ተከብሯል።

 

በ2017 በጀት ዓመት ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመኾን የሕፃናትን ደኅንነት የሚያስጠብቁ ተግባራት መከናወናቸውን የአሥተዳደሩ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኀላፊ በለጥሽ ግርማ ተናግረዋል።

 

ሕፃናትን መንከባከብ፣ መደገፍ እና ደኅንነታቸውን ማስጠበቅ ዓመቱን ጠብቀን የምንገናኝበት ሳይኾን በየጊዜው የምንከውነው ተግባር ሊኾን እንደሚገባም አስረድተዋል።

 

ሕፃናትን መንከባከብ፣ መደገፍ እና ደኅንነታቸውን ማስጠበቅ የነገ ሀገር ተረካቢዎችን የማፍራት ርምጃ መኾኑን የተናገሩት ደግሞ የከተማ አሥተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ ናቸው።

 

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሕፃናት መብት እና ደኅንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አሻግሬ ዘውዴ ከተማ አሥተዳደሩ ለሕፃናት ደኅንነት መጠበቅ የሠጠውን ትኩረት አድንቀዋል።

 

ከሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ባንቲደሩ አጥናፉ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሕፃናትን መብት እና ደኅንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ርምጃዎች መወሠዳቸውን ጠቁመዋል።

 

የሀገር ዉስጥ ጉዲፍቻን በማበረታታት ልጆች በሀገራቸው እንዲያድጉ እየተደረገ መኾኑንም ጠቁመዋል።

 

በአፍሪካ ለ35ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ የሚከበረውን የአፍሪካ ሕፃናት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች በከተማዋ እየተከበረ ነው።

 

ዘጋቢ:- ብርቱካን ማሞ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleበኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት 30 ሚሊዮን ማሳዎች ተለክተው ዘመናዊ የይዞታ ማረጋገጫ ተሠርቶላቸዋል።
Next articleለታላቁ ዩኒቨርስቲ ታላላቅ ፕሮጀክቶች።