ለሁለተናዊ ልማት እና ብልጽግና ገቢን በአግባቡ መሠብሠብ ይገባል።

15

ወልድያ፡ ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የግብር አሠባሠብ ሥርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ በወልድያ ከተማ የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

ከ2017 በጀት ዓመት የግብር አሠባሠብ ግምገማ አኳያ የ2018 በጀት ዓመት የግብር አሠባሠብን ማሻሻል እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል።

የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር የሥራ ኀላፊዎች ያቀዱትን የልማት ሥራ ለማሳካት በተጠናከረ መልኩ ግብር ለመሠብሠብ ማቀዳቸውን ገልጸዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኀላፊ አወቀ ደሳለው በ2017 በጀት ዓመት ከመደበኛ 93 በመቶ እና ከከተማ አገልግሎት 54 በመቶ ገቢ ተሠብሥቧል ብለዋል።

በአፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ ዓመት የታቀደውን ገቢ መሠብሠብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመኾኑም የደረጃ “ሐ” ግብር ከፋዮች እስከ ሐምሌ 2/2017 ዓ.ም ድረስ ከፍለው የሚያጠናቅቁበት አሠራር ከወዲሁ እየተሠራ ነው ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር በዞኑ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሠሩ መኾኑን ገልጸዋል።

ለሁንተናዊ ልማት እና ብልጽግና ገቢን በአግባቡ መሠብሠብ እንደሚያስፈልግም ነው የተናገሩት።

የቀጣይ በጀት ዓመት ግብርም በአግባቡ እንዲሠበሠብ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

በመድረኩ የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር መሪዎች እንዲሁም የገቢ ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleአንፃራዊ ሰላሙ ወደ ተሟላ ሰላም እንዲሸጋገር የሰላም ግንባታ ሥራዎች መቀጠል ይገባቸዋል።
Next articleበማኅበረሰቡ ችግኞችን የማልማት ልምድ እያደገ መጥቷል።