እንጅባራ፡ ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት 4ኛ ዙር 32ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
ምክር ቤቱ በአንድ ቀን ውሎው የሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም የገቢዎች መምሪያን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ገምግሞ አጽድቋል።
የአዊ ብሔረሰብ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሙሉዓዳም እጅጉ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር አሁን ያለው አንፃራዊ ሰላም ዘላቂነቱ እንዲረጋገጥ የምክር ቤት አባላት የሰላም ባለቤት በመኾን የሕዝብ ውክልናቸውን በአግባቡ ሊወጡ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አንፃራዊ ሰላም እንዲሰፍን ላደረጉ ለመላው የጸጥታ መዋቅር፣ ለመሪዎች እና ለሰላም ወዳዱ ሕዝብ ምሥጋና አቅርበዋል።
እንደ ሀገር የተጀመረው የለውጥ ጉዞ ከዳር እንዲደርስ የሰላም ግንባታ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸውም አንስተዋል።
ብሔረሰብ አሥተዳደሩ ሰፊ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው ያሉት አፈጉባኤዋ ያለውን ፀጋ በመጠቀም የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
በአገልግሎት አሰጣጡ የሚስተዋሉ የመልካም አሥተዳደር ችግሮች በቀጣይ መፈታት እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።
ለመኸር ሰብል ልማት የግብዓት ስርጭትን ማሳለጥ እና የአርሶ አደሮችን የእርሻ እንቅስቃሴ በቅርበት መደገፍ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ጉባኤው ለግብርና መምሪያ ኀላፊነት በእጩነት የቀረቡትን የወይዘሮ ቤዛዊት ጌታሁንን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቅቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን