ዩኒዬኖችን በማቀናጀት አቅማቸውን የማሳደግ ሥራ እየተሠራ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን ገለጸ።

5
ወልድያ: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ኅብረት ሥራ ማስፋፊያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሀብታሙ እባቡ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሪፎርም በመተግበር አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ እየተሠራ ነው ብለዋል።
በዞኑ 380 ሺህ 591 አባላትን ያቀፉ 574 መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማኅበራት እና አምስት ዩኒዬኖች ይገኛሉ ብለዋል። የአባላቱን ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ በኢኮኖሚው ውስጥ ያላቸውን ሚና ለማጎልበት ማኅበራትን በማዋሐድ እና በማሻሻል በአዲስ መልክ እንዲደራጁ እየተደረገ መኾኑን አስረድተዋል።
አነስተኛ ማኅበራትን በማቀናጀት ግዙፍ ዩኒዬኖች የማድረግ ሂደቱ የፋይናንስ አቅማቸውን እና የአባላት ጥራትን በማሳደግ አገልግሎታቸውን ለማስፋት ሚናው ጉልህ መኾኑንም አስረድተዋል።
የሰሜን ወሎ ዞን ምክትል አሥተዳዳሪ እና የንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ ታምራት ንጋቱ ዩኒዬኖች አቅማቸውን በማሳደግ ኅብረተሰቡን እንዲያገለግሉ አሳስበዋል። ዞን አሥተዳደሩም የተዋሐዱ ማኅበራት የተጠናከረ አቅም ኖሯቸው የሕዝብን ችግር እንዲፈቱ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየጤና አጠባበቅ ጣቢያዎችን የአገልግሎት አሰጣጥ ለማሻሻል እየሠራ መኾኑን የምዕራብ ጎጃም ዞን አስታወቀ።
Next articleየተጠባባቂ ጥሪ ማስታወቂያ