
ወልድያ: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ የ11 ወራት የሥራ አፈፃፀሙን ገምግሟል። የዞኑ ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኀላፊ ሙሉ አዲሴ መንግሥት ሠራተኞች ባለፉት 11 ወራት በጸጥታ ችግር ውስጥም ኾነው የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ኅብረተሰቡን ማገልገላቸውን ጠቅሰዋል።
ሕዝብን በማገልገል እና ሰላምን በማስፈን ረገድ ጉልህ ድርሻ መወጣታቸውንም ነው ያስረዱት።በተለይም የሰው ኀይል ስምሪቱ በውድድር ሕጉ እንዲፈጸም በልዩ ሁኔታ እየተገመገ መመራቱን ገልጸዋል።
ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ማጣራት ሥራ ተጀምሯል ብለዋል ኀላፊዋ። ሀሰተኛ የሥራ ልምድ፣ የሕክምና ማስረጃ እና የደኅንነት ስጋት ማስረጃዎችም የማጣራት ሥራ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ሁሉም የወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ሲቪል ሰርቪስ ጽሕፈት ቤት ኀላፊዎች እና ቡድን መሪዎች በግምገማ መድረኩ ተገኝተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን