
ደብረ ብርሃን: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በከተማው የመንግሥት
ሠራተኞች የሕፃናት ማቆያ ባለመኖሩ ሠራተኞች ይቸገሩ እንደነበር አንስተዋል።
ይህ ማዕከል ተገንብቶ ሲጠናቀቅም የአገልግሎት አሰጣጡን የበለጠ በማቀላጠፍ በኩል የሚጫወተው ሚና ቀላል አይኾንም ብለዋል።ይህ ማዕከል በ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር በጀት የሚገነባ መኾኑንም ተናግረዋል።
የሚገነባው የሕፃናት ማቆያ በ2018 ዓ.ም በአጭር ጊዜ ተገንብቶ በዚያው ዓመት አገልግሎት እንዲሰጥ እናደርጋለን ብለዋል ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው።
ግንባታውን የሚቆጣጠረው የከተማ አሥተዳደሩ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ መምሪያ ነው። የመምሪያው ኀላፊ በለጥሽ ግርማ ይህ ተግባር በተለይም የሴት የመንግሥት ሠራተኞችን ተደራራቢ ጫና የሚያቃልል ነው ብለዋል።
ግንባታው በተያዘለት የጊዜ ገደብ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት እንዲያስችል ተገቢውን ድጋፍ እና ክትትል እናደርጋለን ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ብርቱካን ማሞ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን