ዘላቂ ሰላምን ለማጽናት ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት ጠየቀ።

5
ደብረ ታቦር: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ አራተኛ ዙር፣ 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 43ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።
ምክር ቤቱ የ2017 ዓ.ም ሦስተኛ ሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸምን በገመገመበት ጉባኤው ሰላምን ማጽናት ዋነኛ አጀንዳው አድርጎ ተወያይቷል። በውይይቱም የታዩ ክፍተቶች እንዲሻሻሉ፣ ጥንካሬዎችም እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጧል።
የሁሉም የሥራ ዘርፍ እንቅስቃሴ እና እድገት መሠረቱ ሰላም ሲኖር መኾኑን የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል። የመጣውን አንፃራዊ ሰላም ማጽናት ይገባልም ብለዋል።
እስከ ቀበሌ ወርዶ ሕዝብን አደራጅቶ በመሥራት ሰላምን ማጽናት እንደሚገባ ተናግረዋል። የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቄስ መልካሙ ላቀው “የሰላም ጉዳይ ውስን ለኾነ አካል ብቻ የሚገፋ አይደለም፤ በመኾኑም ሁሉም የድርሻውን መወጣት አለበት” ብለዋል።
የተጀመሩ መሠረተ ልማቶች ተጠናቀው ለኅብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጡ የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት።የሰላም እጦቱ እንቅፋት እንደኾነ ያነሱት አፈ ጉባኤው ሁሉም “ለሰላም ዘወትር ተግቶ በመሥራት የልማት ጉዞን ማፋጠን ይገባል” ብለዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ደሴ መኮንን የከተማዋ ሰላም በተሻለ ለውጥ ላይ መኾኑን አንስተዋል። የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ማጠናቀቅ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የመጣውን ሰላም በማረጋገጥ የተዳከመውን የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንዲያንሰራራ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል። የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ለባለሀብቶች ጥሪ ቀርቧል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ቃል በተግባር ተፈጽሞልናል” ቤታቸው የታደሰላቸው አቅመ ደካሞች
Next articleለደብረ ብርሃን ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች የሕፃናት ማቆያ ማዕከል ለመገንባት የመሰረተ ድንጋይ ተቀመጠ።