ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚቢሽን ክፍልን በይፋ ከፈቱ።

14
ባሕር ዳር: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚቢሽን ክፍልን በይፋ ከፍተዋል።
ይኽ ድንቅ ክንውን በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የዓየር ንብረት ለውጥ እና የኢትዮጵያ ምላሽ፣ ግብርና፣ የውኃ ኃይል እና ኢነርጂ፣ ኤሮኖቲክስ እና አቪየሽን ላይ ያተኮሩ አምስት የዐውደ ርዕይ ምድቦችን የያዘ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ሙዚየሙ ሀገራችን ሳይንስ እና ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ያላትን ጽኑ ፍላጎት የሚያሳይ እንደሆነም ነው የተጠቆመው።በተጨማሪም በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነው የሕዋ ቅርጽ ሉላዊ የትዕይንት አዳራሽም በዚሁ አውደርዕይ ይፋ ሆኗል።
በ1 ሺህ ስኩዌር ሜትር እና 36 ሜትር ዲያሜትር ይዞ ያረፈው አዳራሽ ዘመኑን በዋጀ የ4K ዲጂታል ምስል (ጥራት) ማሳያ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት ነውም ተብሏል።
ምስለ ሕዋው ከፍተኛ ጥራት ያለው እጅግ አስደማሚ ምስሎችን በማቅረብ የሕዋውን ዓለም እጅግ አቅርቦ የሚያሳይም ነው።ዕውቀት ለማሰስ፣ ለመማር እና ለመነሳሳት ምቹ የሆነው የሳይንስ ሙዚየም ለጎብኝዎች ክፍት ሆኗል።
ኢትዮጵያውያን በሙዚየሙ ተገኝተው የኢትዮጵያን የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መፃዒ ተስፋ እንዲመለከቱም ተጋብዘዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ኅብረተሰቡ ሰላምን በማፅናት ወደ ልማት የመግባት ቁርጠኛ አቋም ይዟል” ሰሜን ወሎ ዞን
Next article“ቃል በተግባር ተፈጽሞልናል” ቤታቸው የታደሰላቸው አቅመ ደካሞች