“ኅብረተሰቡ ሰላምን በማፅናት ወደ ልማት የመግባት ቁርጠኛ አቋም ይዟል” ሰሜን ወሎ ዞን

18

ወልድያ: ሰኔ 07/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ወቅታዊ የሰላም፣ የሕግ ማስከበር፣ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር የ11 ወራት ሥራዎችን ገምግሟል።

የጸጥታ መዋቅሩ ሕግ ለማስከበር በቅንጅት የተሻለ ተግባር ፈጽሟል፤ በዚህም የዞኑን ሰላም የማፅናት ሥራ ምቹ ኹኔታን መፍጠር እንደተቻለ በመወያያ ሰነዱ ተጠቅሷል።

የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር እንደ ልብ ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በነበሩ 52 ቀበሌዎች ኅብረተሰቡን የማነጋገር፣ መዋቅር የመፍጠር እና ኅብረተሰቡ ወደ ልማት እንዲገባ የማድረግ ሥራ ተሠርቷል።

ከፍተኛ የክልል የሥራ ኀላፊዎች በሕዝብ ግንኙነት መድረኮች ተሳትፈዋል ነው ያሉት።

ኅብረተሰቡም ሰላምን በማፅናት በሙሉ አቅሙ ወደ ልማት የመግባት ቁርጠኛ አቋም ይዟል፤ መሪዎችም በኀላፊነት ሕዝቡን በማስተባበር አካባቢውን የመጠበቅ እና የመልካም አሥተዳደር ችግሮችን የመቅረፍ ሥራ ይሠራሉ ብለዋል።

ባለፉት አሥራ አንድ ወራት 155 የካፒል ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለምረቃ ዝግጁ ኾነዋል፤ 173 ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ ናቸው ነው ያሉት።

እስከ ሰኔ 30 ቀሪ ተግባራትን የመፈጸም እና ለ2018 በጀት ዓመት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ይተገበራሉ ነው ያሉት።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ከድር ሙስጠፋ ማኅበረሰቡ የሰላሙም የልማቱም ባለቤት ኾኗል ብለዋል።

በአስራ አንድ ወራት ውስጥ ከፅንፈኝነት ጋር ያለው ችግር የተስተካከለ፣ ማኅበረሰቡም እየተረዳ እና ሕግ ማስከበሩን እየደገፈ አካባቢውን ተደራጅቶ እንዲጠብቅ ተደርጓል ነው ያሉት።

መሪውንም የማጥራት እና የማብቃት ተግባር መሠራቱን ተናግረዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየተማሪዎች ክልላዊ ፈተና እና የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ገለጸ፡፡
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የሳይንስ ሙዚየም ቋሚ ኤግዚቢሽን ክፍልን በይፋ ከፈቱ።