መንግሥት ሠራተኞችን አቅም በማዘመን ኅብረተሰቡን በቅንነት ለማገልገል የሚያስችል ሪፎርም እየተሠራ መኾኑን የሰሜን ወሎ ዞን አስታወቀ።

23

ወልድያ: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ የመንግሥት አሥተዳደር አገልግሎት ሪፎርም የትግበራ ንቅናቄ መድረክ አካሂዷል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር የመንግሥት ሠራተኞች ወቅቱ የሚጠይቀውን ሁለንተናዊ አቅም ያጎለበቱ ሊኾን ይገባል ብለዋል። ይህ ካልኾነ የተገልጋዩን ኅብረተሰብ ተለዋዋጭ የአገልግሎት ፍላጎት ማርካት አይቻልም ነው ያሉት።

በቴክኖሎጂ አገልግሎት የመስጠት አቅምን መገንባት አስፈላጊ ኾኖ ተገኝቷል ያሉት አሥተዳዳሪው የሥራ ኀላፊዎች አፈጻጸሙን በትኩረት እየተከታተሉ ይደግፋሉ ብለዋል።

ለዚህም መንግሥት ሠራተኞች በክህሎት እና በአቅማቸው ልክ ማገልገል ስላለባቸው ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ሂደቱን ከሥራ ኀላፊዎች ተጀምሯል። በሂደት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ እንደሚፈተሽ ገልጸዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኀላፊ ሙሉ አዲሴ የመንግሥት ሠራተኞች ባለ አቅማቸው ኅብረተሰቡን ሲያገለግሉ ኖረዋል፤ አሁንም በግጭት ውስጥ ኾነው መንግሥትን የማፅናት ቁርጠኛ ተግባር እየፈፀሙ ነው ብለዋል።

የመንግሥት ሠራተኞችን አቅም በማዘመን ኅብረተሰቡን በቅንነት ለማገልገል የሚያስችል ሪፎርም ይደረጋል፤ የሠራተኞችን መረጃ ዲጂታል በማድረግ በዳታ ቤዝ እንዲያዝ ኾኗል ነው ያሉት።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነጻ የዐይን ሞራ ግርዶሽ ሕክምና እየሠጠ ነው።
Next articleሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች ተሠርተዋል።