ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሦስተኛው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ “ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበር እና ለአብሮነት” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
የሐረሪ ክልል ደግሞ አራተኛውን የሃይማኖት ተቋማት ኮንፈረንስ ለማካሄድ ኀላፊነቱን ከአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተረክቧል።
የሐረሪ ክልል የመቻቻል፣ የፍቅር እና የሰላም ተምሳሌት እንደኾነ ይነገራል። የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ኮንፈረንስ መላው ኢትዮጵያውያንን በማገናኘት ሰላም እና አንድነት እንዲጸና ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
የአማራ ክልል የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር ያካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ የሰላም መልዕክቶች የተላለፉበት፣ ስለ ሀገር ሰላም የተጸለየበት እና የተመከረበት ኾኖ ተጠናቅቋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን