
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበር እና ለአብሮነት” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
በጉባኤው የባሕር ዳር እና ደሴ ሀገረ ስብከት ካቶሊካዊ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ባስተላለፉት መልዕክት ከቻላችሁስ ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ጠቅሰው እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ፈጣሪ የሰጠንን ትዕዛዝ ማክበር አለብን ብለዋል።
እርስ በእርስ ለፍቅር እና ለመልካም ምግባር የመትጋትን አስፈላጊነት የሃይማኖት አስተምህሮዎች እንደሚሰብኩም ተናግረዋል።
ለሰላም መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ መኾን ከኛ ይጠበቃልም ነው ያሉት ብጹዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ።
ዘጋቢ፦ ዋሴ ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን