
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ሦስተኛው ሀገር አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ “ሃይማኖቶች ለሰላም፣ ለመከባበር እና ለአብሮነት” በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
በጉባኤው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን ፕሬዝዳንት እና የኢትጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ ፓስተር ታደሰ አዱኛ ምድሯ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ መኾኗን ገልጸዋል። የሕዝቦች የሰላም እጦት ምክንያት ደግሞ በፈጣሪ ሕግ አለመታዘዝ የመጣ መኾኑን ነው ያስገነዘቡት።
“ፈጣሪ ያልተገኘበት የትኛውም ሥራ ውጤታማ አይደለም፤ የምንሠራው ሥራ ለፈጣሪ የሚያስደስት ባለመኾኑ የሰው ልጆች በችግር ውስጥ እንዲወድቁ ኾኗል፤ መፍትሔው የሰላም ምንጭ ወደኾነው ወደ ቃሉ መመለስ ይገባል” ብለዋል።
ጥላቻ የችግር ምንጭ እና የሰላም አሜኬላ በመኾኑ ተቀራርቦ መነጋገር፣ ተወቃቅሶ ችግሮችን መፍታት እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
በመረዳዳት፣ በመተጋገዝ፣ በመከባበር ሀገርን መጠበቅ ከዚህ ትውልድ ይጠበቃልም ብለዋል።
“ሰላም በምድሪቱ እንዲሰፍን ወደ ፈጣሪ እንመለስ፤ ለሕጉም እንታዘዝ፤ እርስ በእርስ እንፈቃቀር” ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን