
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው ሦስተኛው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ተጠናቅቋል።
በጉባኤው የማጠቃለያ ዝግጅት ላይ የተለያዩ አካላት ዕውቅና እና ምሥጋና አግኝተዋል።
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለክልሉ እና ለሀገር ሰላም ጠንካራ ሥራዎችን እያከናወኑ መኾኑ እና በተለይም በአማራ ክልል ተከስቶ የነበረው ግጭት ተፈትቶ አንጻራዊ ሰላም እንዲመጣ አበርክቷቸው የላቀ እንደነበር ተመላክቷል።
ሦስተኛው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ በተሳካ ሁኔታ እንዲከናወንም ርእሰ መሥተዳድሩ ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበራቸው ተጠቅሶ ለዚህም አገልግሎታቸው የሚመጥን ሜዳሊያ ተሸልመዋል።
ሜዳሊያውን የጉባኤው የበላይ ጠባቂ ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች አበርክተውላቸዋል።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን