
እንጅባራ: ሰኔ 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር 8894 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከዛሬ ሰኔ 5/2017 ዓ.ም ጀምሮ ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።
የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ደስታው አለሙ ፈተናው በ183 የፈተና መስጫ ጣቢያዎች እየተሰጠ መኾኑን ተናግረዋል። ፈተናውን የሚያሥተዳድሩ ከ550 በላይ የፈተና አሥፈጻሚዎች መመደባቸውንም ገልጸዋል።
በጸጥታ አካላት፣ በትምህርት መዋቅሩ፣ በኅብረተሰቡ እና በአሥተዳደር መዋቅር የጋራ ጥረት ለሁለት ቀናት ሲሰጥ የቆየው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ያነሱት ኀላፊው ለ6ኛ ክፍል ፈተና ስኬታማነት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩም ጠይቀዋል።
በጸጥታ ችግር ምክንያት ትምህርታቸውን ዘግይተው የጀመሩ 912 ተማሪዎች ደግሞ በቀጣይ የክልሉ ትምህርት ቢሮ በሚያወጣው መርሐ ግብር ፈተናቸውን የሚወስዱ ይኾናል ተብሏል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን